በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ቭላዲሚር አሉሽኪን እና ባለቤቱ ታትያና

መስከረም 16, 2020
ሩሲያ

ወንድም ቭላዲሚር አሉሽኪን ወደ እስር ቤት አይመለስም

ወንድም ቭላዲሚር አሉሽኪን ወደ እስር ቤት አይመለስም

የፔንዛ ክልላዊ ፍርድ ቤት ወንድም አሉሽኪን፣ ወንድም ኩልያሶቭ፣ ወንድም ማግሊቭ፣ ወንድም ቲሞሺን፣ እህት አሉሽኪና እና እህት ኦልኮቫ ያቀረቡትን ይግባኝ ተመልክቶ መስከረም 16, 2020 ውሳኔውን አሳወቀ። ፍርድ ቤቱ ቀደም ሲል በወንድም አሉሽኪን ላይ የተላለፈው የስድስት ዓመት እስር ወደ አራት ዓመት እስር በገደብ እንዲቀየርና እንዲፈታ ወስኗል። ወንድም አሉሽኪን ወደ እስር ቤት እንደማይመለስ በማወቃችን ተደስተናል። በሌሎቹ ላይ ግን መጀመሪያ የተላለፈው የእስር በገደብ ፍርድ በዚያው እንዲጸና ተወስኗል።