በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ኒኮላይ ቮይሽቼቭ

መስከረም 27, 2023
ሩሲያ

ወንድም ኒኮላይ ቮይሽቼቭ የሦስት ዓመት እስራት ተፈረደበት

ወንድም ኒኮላይ ቮይሽቼቭ የሦስት ዓመት እስራት ተፈረደበት

መስከረም 14, 2023 በአድግያ ሪፑብሊክ የማይኮፕ ከተማ ፍርድ ቤት፣ ወንድም ኒኮላይ ቮይሽቼቭን ጥፋተኛ ነው በማለት የሦስት ዓመት እስራት ፈርዶበታል። ከጥቅምት 20, 2022 ጀምሮ በማረፊያ ቤት የቆየ ሲሆን አሁንም እስራቱ ይቀጥላል።

አጭር መግለጫ

ኒኮላይ መታሰሩን መስማታችን ቢያሳዝነንም ይሖዋ ለእሱም ሆነ መከራ እየደረሰባቸው ላሉት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ሁሉ ብርታትና መጽናናት እንደሚሰጣቸው እርግጠኞች ነን።—መዝሙር 119:76

የክሱ ሂደት

  1. ጥቅምት 19, 2022

    የክስ ፋይል ተከፈተበት

  2. ጥቅምት 20, 2022

    ቤቱ ተፈተሸ፤ ምርመራ ተካሄደበት እንዲሁም ጣቢያ እንዲቆይ ተደረገ

  3. ጥቅምት 21, 2022

    ወደ ማረፊያ ቤት ተዘዋወረ

  4. ጥር 11, 2023

    ኒኮላይ የጤና ችግር ያለበት በመሆኑ ከማረፊያ ቤት ወደ ቁም እስር እንዲዛወር ለዳኛው አቤቱታ ቀረበ። አቤቱታው ውድቅ ተደረገ እንዲሁም ማረፊያ ቤት የሚቆይበት ጊዜ እንዲራዘም ተወሰነ

  5. ጥር 25, 2023

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

  6. መስከረም 14, 2023

    ጥፋተኛ ነው ተብሎ የሦስት ዓመት እስር ተፈረደበት

a ወንድም ኒኮላይ ማረፊያ ቤት ስለነበረ ቃለ መጠይቅ ሊደረግለት አልተቻለም።