በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም አሌክሲ ቡደንቹክ ከወንድ ልጁ ከዬጎር፣ ከሴት ልጁ ከሶፊያ እና ከባለቤቱ ከታትያና ጋር

ሐምሌ 7, 2021
ሩሲያ

ወንድም አሌክሲ ቡደንቹክ ከሩሲያ እስር ቤት ተለቀቀ

ወንድም አሌክሲ ቡደንቹክ ከሩሲያ እስር ቤት ተለቀቀ

ወንድም አሌክሲ ቡደንቹክ ሐምሌ 6, 2021 የእስር ጊዜውን ጨርሶ በኦረንበርግ ከተማ ከሚገኘው ወህኒ ቤት ተፈቷል። አሌክሲ መስከረም 2019 ከታሰሩት በሳራቶቭ ከተማ የሚኖሩ ስድስት ወንድሞች አንዱ ነው። በአሁኑ ወቅት ሦስቱ እስር ቤት ይገኛሉ። አሌክሲ በተፈታበት ወቅት ቤተሰቦቹና ጓደኞቹ እሱን ለመቀበል ከ800 ኪሎ ሜትር በላይ ተጉዘዋል። ከዚህ በኋላ በሳራቶቭ ወደሚገኘው ቤቱ ተመልሶ ከቤተሰቡ ጋር ይቀላቀላል።