በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ከግራ ወደ ቀኝ፦ የአንድሬ ልጅ አልቢና፣ ባለቤቱ ስቬትላና፣ አንድሬ አንድሬዬቭ፣ ልጁ አንዤሊካ እና ባለቤቷ አናቶሊ፤ ውስጠኛው ፎቶግራፍ፦ ወንድም አንድሬ ከእስር ተለቅቆ ከባለቤቱ ጋር ሲገናኝ

የካቲት 27, 2023
ሩሲያ

ወንድም አንድሬ አንድሬዬቭ ከሩሲያ ወህኒ ቤት ተለቀቀ

ወንድም አንድሬ አንድሬዬቭ ከሩሲያ ወህኒ ቤት ተለቀቀ

የካቲት 22, 2023 ወንድም አንድሬ አንድሬዬቭ ከሩሲያ ወህኒ ቤት ተለቅቋል፤ አንድሬ ከታሰረ ሦስት ዓመት አልፎታል።

ጥቅምት 16, 2019 ባለሥልጣናቱ በኩርስክ የሚገኙ በርካታ የይሖዋ ምሥክሮችን ቤቶች የበረበሩ ሲሆን በወንድሞቻችን ላይ ምርመራ አካሂደው ነበር፤ አንድሬ እና ሌሎች ወንድሞች በቁጥጥር ሥር የዋሉት ይህን ተከትሎ ነው። አንድሬ ማረፊያ ቤት አንድ ዓመት ከስምንት ወር ገደማ ካሳለፈ በኋላ ሰኔ 3, 2021 እስራት ተፈረደበት

አንድሬ በእምነቱ ምክንያት ታስሮ በነበረበት ወቅት፣ የባለቤቱን የስቬትላናን እንዲሁም አንዤሊካ እና አልቢና የተባሉትን ሁለት ሴቶች ልጆቻቸውን መንፈሳዊነት ለማጠናከር የሚችለውን ሁሉ ያደርግ ነበር። በደብዳቤዎቹ አማካኝነት አዘውትሮ መንፈሳዊ ማበረታቻ ይሰጣቸው ነበር። እንዲያውም ለአንዤሊካ የጋብቻ ንግግሯን ጽፎላታል፤ እሷና ባለቤቷ የጋብቻ ሥነ ሥርዓታቸው የፈጸሙት አንድሬ ታስሮ በነበረበት ወቅት ነው። አንዤሊካ እንዲህ ብላለች፦ “በጣም ግሩምና ልብ የሚነካ ንግግር ነው ያዘጋጀው። እንግዶቹ ሁሉ ልባቸው በጥልቅ ተነክቷል፤ . . . እኛም በዕለቱ በቦታው አብሮን የተገኘ ያህል ተሰምቶናል።”

አንድሬ የታሰረው በባቡር የስምንት ሰዓት መንገድ ርቆ ስለነበር ቤተሰቡ እሱን ለመጠየቅ ረጅም መንገድ መጓዝ ነበረባቸው። ጉዞው አድካሚ ቢሆንም ስቬትላና እንደገለጸችው የአካባቢው ወንድሞች እሷንም ሆነ ልጆቿን ሁልጊዜ ይደግፏቸው ነበር፤ ማረፊያ፣ ምግብ እንዲሁም ወደ እስር ቤት የሚወስዳቸውና የሚመልሳቸው መጓጓዣ ያዘጋጁላቸው ነበር። እንዲያውም አንዳንዶች፣ ሌሊት ጀምሮ በመሰለፍ የአንድሬ ቤተሰብ እሱን ለመጠየቅ ተራ እንዲደርሳቸው ወረፋ ይይዙላቸው ነበር።

ወንድም አንድሬ ከእስር ሲለቀቅ ሊቀበሉት የመጡ ወዳጅ ዘመዶቹ

አንድሬ እስር ቤት በደረሰበት እንግልት ሰውነቱ ቢጎዳም መንፈሳዊነቱ አሁንም ጠንካራ ነው። መልካም ምግባሩና ክርስቲያናዊ ባሕርያቱ በእስር ቤቱ ኃላፊዎች ዘንድ አክብሮት አትርፈውለታል፤ በመሆኑም ለሌሎች ከሚፈቀደው በላይ ሰዎች እንዲጠይቁት ተፈቅዶለታል። አንድሬ እስራቱን በተመለከተ እንዲህ ብሏል፦ “በደረሰብኝ ነገር ንዴትም ሆነ ምሬት አላደረብኝም፤ ለማንም ቢሆን ጥላቻ የለኝም። በአምላክ እርዳታ ታማኝነቴን መጠበቅ ችያለሁ፤ በዚህም ደስተኛ ነኝ።”

አንድሬ ክርስቲያናዊ ፍቅር ለማሳየት ያለውን ቁርጠኝነት ይሖዋ አብዝቶ እንደሚባርክለት እንተማመናለን።—1 ዮሐንስ 4:16