ነሐሴ 3, 2021
ሩሲያ
ወንድም አንድሬ ኦክሪምቹክ ይሖዋ በሚሰጠው ብርታት ታምኗል
ወቅታዊ መረጃ | የካቲት 3, 2022 አራተኛው ጠቅላይ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት፣ ወንድም አንድሬ ኦክሪምቹክ ያቀረበውን አቤቱታ ውድቅ አድርጎታል። መጀመሪያ ላይ የተላለፈበት የአራት ዓመት የገደብ እስራት ብይን ይጸናል። እርግጥ ወንድም አንድሬ አሁን ወህኒ አይወርድም።
የክሱ ሂደት
ግንቦት 22, 2019
ጭምብል ያጠለቁ ፖሊሶች በማለዳ የአንድሬን ቤትና መኪና ፈተሹ
ጥቅምት 29, 2020
የወንጀል ክስ ተመሠረተበት። ሕገ ወጥ በሆነ ሃይማኖታዊ ስብሰባ ላይ በመገኘትና ጽንፈኛ የሆነ ድርጅት የሚያካሂዳቸውን እንቅስቃሴዎች በመደገፍ ወንጀል ተከሰሰ
ሚያዝያ 5, 2021
ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ
ነሐሴ 2, 2021
በሮስቶቭ-ኦን-ዶን ከተማ የሚገኘው የሌኒንስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ አንድሬ ጥፋተኛ ነው የሚል ውሳኔ አሳለፈ። ፍርድ ቤቱ የአራት ዓመት የገደብ እስር ፈርዶበታል
ጥቅምት 4, 2021
የሮስቶቭ ክልላዊ ፍርድ ቤት አንድሬ ያቀረበውን ይግባኝ ውድቅ አደረገ። መጀመሪያ ላይ የተላለፈበት ብይን በዚያው ይጸናል
አጭር መግለጫ
በሩሲያ ያሉ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የሚያሳዩት ጠንካራ እምነት ለሁላችንም ግሩም ምሳሌ ይሆናል። አንድሬና ቤተሰቡ በሰማዩ አባታችን በይሖዋ ሙሉ በሙሉ በመታመን ይህን ፈተና በጽናት እንደሚወጡት እርግጠኞች ነን።—መዝሙር 37:5