በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም አንድሬ ዳንዬልያን እና ባለቤቱ ኒና

ኅዳር 9, 2022
ሩሲያ

ወንድም አንድሬ ዳንዬልያን የስድስት ዓመት እስራት ተፈረደበት

ወንድም አንድሬ ዳንዬልያን የስድስት ዓመት እስራት ተፈረደበት

ኅዳር 7, 2022 በአልታይ ግዛት የሚገኘው የሩብትሶቭስኪ ከተማ ፍርድ ቤት ወንድም አንድሬ ዳንዬልያን በስድስት ዓመት እስራት እንዲቀጣ ወስኗል። ወዲያውኑ ወደ እስር ቤት ተወስዷል።

የክሱ ሂደት

  1. ግንቦት 25, 2021

    ፖሊሶች የአንድሬን ስልክ በመጥለፍና በሌሎች የስለላ ዘዴዎች ለወራት ሲከታተሉት ከቆዩ በኋላ የወንጀል ክስ መሠረቱበት

  2. ግንቦት 26, 2021

    መኖሪያ ቤቱ ተፈተሸ። አንድሬና ባለቤቱ ጣቢያ ተወስደው ምርመራ ተደረገባቸው። አንድሬ የጉዞ እገዳ ተጣለበት

  3. ሐምሌ 13, 2022

    የጽንፈኛ ድርጅት እንቅስቃሴዎችን አስተባብረሃል በሚል በይፋ ክስ ተመሠረተበት

  4. መስከረም 5, 2022

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

  5. ኅዳር 7, 2022

    የስድስት ዓመት እስራት ተፈረደበት

አጭር መግለጫ

‘ተስፋ የተሰጠውን የወደፊቱን ሕይወት’ በምንጠባበቅበት በአሁኑ ወቅት አንድሬም ሆነ ሌሎች በርካታ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ለአምላክ ያደሩ ሆነው ለመኖር የሚያደርጉትን ጥረት ከልብ እናደንቃለን።—1 ጢሞቴዎስ 4:8

a ወንድም አንድሬ ዳንዬልያን አስተያየቱን የሰጠው ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ በፊት ነው።