በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በኪሮቭ የክልል ፍርድ ቤት ኮሪደር ላይ ወንድም ኦኒስጁክና ባለቤቱ ሲገናኙ

መስከረም 6, 2019
ሩሲያ

ወንድም አንጄይ ኦኒስጁክ ለ11 ወራት ብቻውን ከታሰረ በኋላ ተፈታ

ወንድም አንጄይ ኦኒስጁክ ለ11 ወራት ብቻውን ከታሰረ በኋላ ተፈታ

መስከረም 3, 2019 ወንድም አንጄይ ኦኒስጁክ ከሩሲያ እስር ቤት ተፈታ። ወንድም አንጄይ ኦኒስጁክ በእምነቱ ምክንያት ከጥምቅት 9, 2018 አንስቶ በእስር ቆይቷል። በዚህ ጊዜ ብቻውን ታስሮ የነበረ ሲሆን ባለቤቱን አናን ማግኘትም ሆነ ማነጋገር አይፈቀድለትም ነበር። አሁን ወደ ቤተሰቡ መመለስ ቢችልም ገደቦች ስለተጣሉበት ከሚኖርበት አካባቢ ርቆ መጓዝ አይችልም። የወንጀል ክሱም ቢሆን አልተዘጋም።

በዚህ ሁሉ መከራ መሃል ወንድም አንጄይ ኦኒስጁክና ባለቤቱ ጠንካራ እምነት በማሳየታቸው ደስ ብሎናል። ይሖዋ ‘በእስር’ ላይ ያሉትን ወንድሞች አስመልክቶ የሚቀርቡትን ጸሎቶች በሙሉ የሚሰማ በመሆኑ በጣም አመስጋኞች ነን።—ቆላስይስ 4:2, 3