ሚያዝያ 20, 2023
ሩሲያ
ወንድም ኦካፕኪን የፍጥረት ሥራዎችን መመልከቱ አበርትቶታል
በኢቫኖቮ ክልል የሚገኘው የኪንሸምስኪ ከተማ ፍርድ ቤት ከወንድም አንድሬ ኦካፕኪን ክስ ጋር በተያያዘ በቅርቡ ውሳኔውን ያስተላልፋል ተብሎ ይጠበቃል። አቃቤ ሕጉ እንዲተላለፍበት የሚፈልገውን ብይን ገና አላሳወቀም።
አጭር መግለጫ
እንደ አንድሬ ሁሉ እኛም “የአምላክን ድንቅ ሥራዎች” እናደንቃለን፤ የይሖዋን ፍቅራዊ አሳቢነት እንድናስታውስ ይረዱናል።—ኢዮብ 37:14
የክሱ ሂደት
ኅዳር 18, 2021
በአንድሬ ላይ የክስ ፋይል ተከፈተ
ኅዳር 23, 2021
የአንድሬን ጨምሮ የስድስት የይሖዋ ምሥክሮች ቤቶች ተፈተሹ። አንድሬ በቁጥጥር ሥር ውሎ ጣቢያ እንዲያድር ተደረገ
ኅዳር 24, 2021
የወንጀል ክስ ተመሠረተበት
ኅዳር 25, 2021
ማረፊያ ቤት እንዲወርድ ተደረገ
የካቲት 17, 2022
ከማረፊያ ቤት ተለቀቀ፤ የቁም እስረኛ ተደረገ
ሐምሌ 14, 2022
ከቁም እስር ነፃ ሆነ፤ የጉዞ እገዳ ተጣለበት
ታኅሣሥ 15, 2022
ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ