ሐምሌ 20, 2023
ሩሲያ
ወንድም ዩሪ ሳቨላየቭ ከእስር ቤት ተፈታ
ሐምሌ 19, 2023 ወንድም ዩሪ ሳቨላየቭ በሩብትሶቭስክ ከሚገኝ የሩሲያ እስር ቤት ተፈታ። መጀመሪያ በቁጥጥር ሥር የዋለው ኅዳር 9, 2018 ሲሆን ከአራት ዓመት ተኩል በላይ በእስር አሳልፏል።
እስር ቤቱ ንጽሕና የጎደለው በመሆኑ ወንድም ዩሪ የጤና እክሎች አጋጥመውታል። በተጨማሪም በሐሰት ውንጀላዎች የተነሳ በእስር ቤቱ የቅጣት ክፍሎች ውስጥ በተደጋጋሚ ጊዜ እንዲታሰር ተደርጓል። በእነዚህ ከባድ ሁኔታዎች ውስጥ ቢሆንም እንኳ አዎንታዊ አመለካከት ይዞ መቀጠል ችሏል፤ ይህን ለማድረግ የረዳው በጸሎት በመጽናት ብርታት ማግኘቱ ነው። ዩሪ በመልካም ምግባሩና በክርስቲያናዊ ባሕርያቱ የተነሳ አብረውት በታሰሩት ሰዎችና በእስር ቤቱ ጠባቂዎች ዘንድ አክብሮት አትርፏል።
ፍርድ ቤቱ የእስራት ፍርድ ከማስተላለፉ በፊት ዩሪ ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው ንግግር ላይ ማቴዎስ 22:37ን ነበር፤ በዚህ ጥቅስ ላይ ኢየሱስ “አምላክህን ይሖዋን በሙሉ ልብህ፣ በሙሉ ነፍስህና በሙሉ አእምሮህ ውደድ” ብሎ ነበር። ዩሪ እነዚህን ቃላት በሕይወቱ ተግባራዊ በማድረግና ታማኝነቱን በመጠበቅ ግሩም ምሳሌ
ትቷል። ላሳየው እምነት፣ ፍቅርና ጽናት ይሖዋ እሱን መባረኩን እንደሚቀጥል እንተማመናለን።