በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ዬቭጌኒ ሶኮሎቭ

ሐምሌ 15, 2024
ሩሲያ

ወንድም ዬቭጌኒ ሶኮሎቭ በሁለተኛ የወንጀል ክስ ችሎት ፊት ቀርቦ ተፈረደበት

ወንድም ዬቭጌኒ ሶኮሎቭ በሁለተኛ የወንጀል ክስ ችሎት ፊት ቀርቦ ተፈረደበት

ግንቦት 29, 2024 በአሙር ክልል የሚገኘው የዜይስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ ወንድም ዬቭጌኒ ጥፋተኛ ነው የሚል ብይን ያስተላለፈ ሲሆን የሦስት ዓመት የገደብ እስራት ፈርዶበታል። ወንድም ዬቭጌኒ አሁን ወህኒ አይወርድም።

ይህ በዬቭጌኒ ላይ የቀረበ ሁለተኛው የወንጀል ክስ ነው። የመጀመሪያው ክስ፣ ዬቭጌኒ አሁን በሚኖርባት በቮሮኒሽ ከተማ በሚገኝ ፍርድ ቤት እየታየ ሲሆን በዚህ ክስ ውስጥ እሱና ሌሎች ዘጠኝ ወንድሞች ተካትተዋል።

ዬቭጌኒ ለመጽናት የረዳው ምን እንደሆነ ሲገልጽ እንዲህ ብሏል፦ “ሙሉ በሙሉ በይሖዋ መታመንንና በእሱ መመካትን እየተማርኩ ነው። የትኛውንም ችግር ከይሖዋ በተሻለ መንገድ ልንፈታው አንችልም። ምንጊዜም ቢሆን የእሱ መንገድ ከሁሉ የተሻለና ጥበብ የሚንጸባረቅበት ነው።”

እኛም እንደ ዬቭጌኒ ይሖዋ ምንጊዜም የሚያስፈልገንን እርዳታ እንደሚሰጠን ተማምነን ይሖዋን “አንተ መጠጊያዬ ነህ” ማለታችንን እንቀጥል።​—መዝሙር 142:5

የክሱ ሂደት

  1. ታኅሣሥ 15, 2022

    ዬቭጌኒ ሳያውቅ ሁለተኛ የወንጀል ክስ ተመሠረተበት

  2. መስከረም 22, 2023

    ዬቭጌኒ ሁለተኛ ክስ እንደተመሠረተበት አወቀ። ምርመራ ተደረገበት እንዲሁም “ሃይማኖታዊ ስብሰባ በማዘጋጀትና በመምራት” ወንጀል ተከሰሰ

  3. ሚያዝያ 22, 2024

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

  4. ግንቦት 29, 2024

    ጥፋተኛ ነው ተብሎ የሦስት ዓመት የገደብ እስራት ተፈረደበት