በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የካቲት 12, 2020
ሩሲያ

ወንድም ዬቭጌኒ አክሰኖቭ ከሰዎች ጋር ስለ መጽሐፍ ቅዱስ በመወያየቱ ተከሰሰ

ወንድም ዬቭጌኒ አክሰኖቭ ከሰዎች ጋር ስለ መጽሐፍ ቅዱስ በመወያየቱ ተከሰሰ

በካባረቭስክ ከተማ የዢለዝናዳሮዥኒይ አውራጃ ፍርድ ቤት በወንድም ዬቭጌኒ አክሰኖቭ ላይ የተመሠረተውን ክስ ተመልክቶ ዓርብ፣ የካቲት 14, 2020 ውሳኔ ያስተላልፋል ተብሎ ይጠበቃል። አቃቤ ሕጉ በወንድም አክሰኖቭ ላይ የሦስት ዓመት እስራት እንዲበየንበት ጠይቋል።

ሚያዝያ 21, 2018 ወንድም አክሰኖቭ ከወዳጆቹ ጋር ሆኖ በአንድ ሆቴል የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ እየተወያየ ነበር። የመጽሐፍ ቅዱስ ምክር የቤተሰብን አንድነት የሚያጠናክረው እንዴት እንደሆነ አብረውት ለተሰበሰቡት ሰዎች እየነገራቸው ነበር። በዚህ የተነሳ “ማኅበረሰቡን የሚጎዳ ነገር” በማድረግ እና “የጽንፈኛ ድርጅትን ሥራዎች በማደራጀት” ወንጀል ተከሷል። የፍርድ ቤት ክሱ የጀመረው ጥቅምት 21, 2019 ነበር።

በወንድም አክሰኖቭ ላይ ፍርድ የሚተላለፍበት ቀን ሲቃረብ እሱም ሆነ ቤተሰቡ የይሖዋን እርዳታ መፈለጋቸውን እንዲቀጥሉ እንጸልያለን፤ እንዲሁም ይሖዋ፣ ታማኞቹ “የሚያጡት ነገር” እንደማይኖር የገባውን ቃል እንደሚፈጽም እንተማመናለን።—መዝሙር 34:9