በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የካቲት 10, 2021
ሩሲያ

ወንድም ዴኒስ ክሪስተንሰን በአመክሮ እንዲፈታ የቀረበው ጥያቄ ውድቅ ተደረገ

ወንድም ዴኒስ ክሪስተንሰን በአመክሮ እንዲፈታ የቀረበው ጥያቄ ውድቅ ተደረገ

የካቲት 10, 2021 የኩርስክ ክልላዊ ፍርድ ቤት፣ ወንድም ዴኒስ ክሪስተንሰን የእስር ጊዜውን ሳይጨርስ እንዲለቀቅ የቀረበውን ጥያቄ ውድቅ አደረገ። ወንድም ዴኒስ ክሪስተንሰን፣ ቀሪው የእስር ጊዜ በገንዘብ መቀጮ እንዲቀየርለት ፍርድ ቤቱን ጠይቆ ነበር። ዴኒስ በአመክሮ ለመፈታት ብቁ ከሆነ ከዓመት በላይ ቢሆነውም የሚያቀርበው ጥያቄ በተደጋጋሚ ውድቅ እየተደረገ ነው።

በቅርቡ ዴኒስ ለባለቤቱ ለአይሪና ደብዳቤ ጽፎላት ነበር። በደብዳቤው ላይ በጣም ከሚወዳቸው ጥቅሶች አንዱን ጠቅሶላታል፦ “ካልታከትን ጊዜው ሲደርስ ስለምናጭድ ተስፋ ቆርጠን መልካም ሥራ መሥራታችንን አንተው።” (ገላትያ 6:9) ዴኒስ፣ ሌሎችን በመርዳት መልካም ሥራ መሥራታቸውን ከቀጠሉና ተስፋ ካልቆረጡ ይሖዋ እንደሚክሳቸው እርግጠኛ እንደሆነ ተናግሯል። በተጨማሪም ከእስር ቤት ሲወጣ፣ ወደ እስር ቤት ሲገባ ከነበረው የበለጠ መንፈሳዊ ሆኖ መውጣት እንደሚፈልግ ተናግሯል።

ዴኒስ ከግንቦት 2017 አንስቶ በእስር ላይ ይገኛል፤ በዚህም ምክንያት እሱና ባለቤቱ አይሪና ለአራት ዓመት ያህል ተለያይተው ለመኖር ተገደዋል። ዴኒስና አይሪና በይሖዋ በመታመን፣ ውስጣዊ ሰላምን ጠብቆ በመኖር እንዲሁም ምንም ሳያወላውሉ ታማኝ በመሆን ረገድ ግሩም ምሳሌ ይሆኑናል።—ፊልጵስዩስ 1:14