በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ሐምሌ 11, 2020
ሩሲያ

ወንድም ዴኒስ ክሪስተንሰን ከልዩ የቅጣት ክፍል ወደ መደበኛ እስር ቤት ተዛወረ

ወንድም ዴኒስ ክሪስተንሰን ከልዩ የቅጣት ክፍል ወደ መደበኛ እስር ቤት ተዛወረ

ሐምሌ 11, 2020 የልጎፍ እስር ቤት ወንድም ዴኒስ ክሪስተንሰንን ወደ መደበኛ እስር ቤት አዛውሮታል። ወደዚህ ከመዛወሩ በፊት ለ15 ቀን ያህል በልዩ የቅጣት ክፍል ታስሮ ነበር። ቀደም ሲል ሪፖርት እንደተደረገው፣ ወንድም ክሪስተንሰን ቅጣት የተላለፈበት መሠረተ ቢስ በሆኑ ክሶች ምክንያት ነው። አሁን ግን ወደ መደበኛ እስር ቤት ተዛውሯል። ወንድም ክሪስተንሰን አሁንም አዎንታዊ አመለካከት አለው። እሱን ወክሎ የሚከራከረው የጠበቆች ቡድን መጨረሻ ላይ ከተላለፉት ውሳኔዎች ጋር በተያያዘ ይግባኝ ለመጠየቅ አስበዋል፤ እንዲሁም እነዚህ ውሳኔዎች ወንድም ክሪስተንሰን ከእስር ቀደም ብሎ ለመፈታት ባቀረበው ጥያቄ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደማያሳድሩ ተስፋ ያደርጋሉ።