ነሐሴ 3, 2020
ሩሲያ
ወንድም ጀናዲ ሽፓኮቭስኪ ከእስር ተለቀቀ
ሰኞ፣ ነሐሴ 3, 2020 የፓስኮቭ ክልል ፍርድ ቤት ወንድም ጀናዲ ሽፓኮቭስኪ ከእስር እንዲለቀቅ ወስኗል። ፍርድ ቤቱ ወንድም ጥፋተኛ ነው የሚለው ውሳኔ እንዲጸና ያደረገ ቢሆንም የተፈረደበትን የስድስት ዓመት ተኩል እስር ወደ ገደብ እስር ለውጦለታል፤ ይህም የሁለት ዓመት የክትትል ጊዜን ይጨምራል። በመሆኑም ውሳኔው ከተላለፈ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ወንድም ጀናዲ ሽፓኮቭስኪ ከእስር ተለቋል። አቃቤ ሕግ ውሳኔውን አስመልክቶ ይግባኝ የማለት መብት አለው።