በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ፊሊክስ ማክሃማዲየቭ ከሩሲያ እስር ቤት ከተለቀቀ በኋላ ኡዝቤኪስታን ውስጥ ባለ የባቡር ጣቢያ ከባለቤቱ ከዬቭጌኒያ ጋር ሲገናኝ፣ ጥር 21, 2021

ጥር 21, 2021
ሩሲያ

ወንድም ፊሊክስ ማክሃማዲየቭ ከሩሲያ እስር ቤት ተፈትቶ ወደ ኡዝቤኪስታን እንዲመለስ ተደረገ

ወንድም ፊሊክስ ማክሃማዲየቭ ከሩሲያ እስር ቤት ተፈትቶ ወደ ኡዝቤኪስታን እንዲመለስ ተደረገ

ታኅሣሥ 31, 2020 ወንድም ፊሊክስ ማክሃማዲየቭ ከሩሲያ እስር ቤት ተፈቷል። ወንድም ፊሊክስ ከአገሪቱ እንዲወጣና ወደ ትውልድ አገሩ ኡዝቤኪስታን እንዲመለስ የሚያስችሉት ሰነዶች እስኪሟሉ ድረስ፣ ከአገር የሚባረሩ ሰዎች በሚያርፉበት ቦታ ለጊዜው እንዲቆይ በኦረንበርግ ክልል የሚገኘው የበልያየቭስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ወስኖ ነበር። ይህም የሆነው ወንድም ፊሊክስ ሚያዝያ 2020 የሩሲያ ዜግነቱን ስለተነጠቀ ነው። ጥር 20, 2021 ባለሥልጣናቱ ወንድም ፊሊክስን ወደ ኡዝቤኪስታን በሚሄድ ባቡር ላይ አሳፍረውታል። ወንድም ፊሊክስ ጥር 21, 2021 በሰላም ኡዝቤኪስታን መድረሱን ስንገልጽላችሁ ደስ ይለናል። ባለቤቱ ዬቭጌኒያ ሁለት ቀናት ቀደም ብላ ወደ ኡዝቤኪስታን በመሄድ እዚያ ሲደርስ ተቀብላዋለች።

ፊሊክስ ሩሲያ ውስጥ 18 ዓመት ገደማ ኖሯል። በ2002 ገና ወጣት ሳለ ከእናቱ ጋር ከሳራቶቭ፣ ኡዝቤኪስታን ወደ ሩሲያ መጡ። በ2004 በ19 ዓመቱ ተጠመቀ። በ2011 ከዬቭጌኒያ ጋር ትዳር መሠረተ።

ሰኔ 12, 2018 መሣሪያ የታጠቁና ጭንብል ያጠለቁ የፌደራል ደህንነት አባላት እና ፖሊሶች የፊሊክስን እና የዬቭጌኒያን ቤት በረበሩ። በወቅቱ ፊሊክስ የተያዘ ሲሆን ችሎት ፊት ሳይቀርብ ለአንድ ዓመት ገደማ ታሰረ። ፊሊክስ በጸሎት መጽናቱ ብርታት እንዲያገኝ ረድቶታል። እንዲህ ብሏል፦ “በየቀኑ ይሖዋ ዕለቱን በሰላምና ደስ ብሎኝ እንድውል እንዲረዳኝ እጸልያለሁ።”

ወንድም ፊሊክስ ማክሃማዲየቭ፣ የእስር ቤት ጠባቂዎች ክፉኛ ከደበደቡት ከሁለት ሳምንት ገደማ በኋላ

መስከረም 19, 2019 ፊሊክስና ሌሎች አምስት ወንድሞች ተፈርዶባቸው እስር ቤት ገቡ። ፊሊክስና አራቱ ወንድሞች ያቀረቡት ይግባኝ ተቀባይነት ስላላገኘ ከመኖሪያቸው ከሳራቶቭ 800 ኪሎ ሜትር ርቆ በኦረንበርግ ወደሚገኝ ወህኒ ቤት ተዛወሩ። እስር ቤቱ ሲደርሱም ክፉኛ ተደበደቡ

ፊሊክስ ይህ ሁሉ መከራ ቢደርስበትም አሁንም ደስታውን አላጣም፤ ፈገግታውም አልጠፋም። ዬቭጌኒያ እንዲህ ብላለች፦ “በጣም ኮርቼበታለሁ! የፍርድ ሂደቱን በእርጋታ የተከታተለ ከመሆኑም ሌላ አሁንም በጽናት ቀጥሏል፤ እኔም እንኳ እንድጸና እየረዳኝ ነው።”

የሩሲያ ባለሥልጣናት ፊሊክስን ለመጉዳትና እምነቱን ለማጥፋት ጥረት ቢያደርጉም ለረጅም ጊዜ የዘለቀው ስደት ለይሖዋ ያለውን ታማኝነት እንዳጠናከረለት ገልጿል። ይህ ሁኔታ በዘፍጥረት 50:20 ላይ ዮሴፍ ለወንድሞቹ የተናገረውን የሚከተለውን ሐሳብ ያስታውሰናል፦ “ምንም እንኳ እኔን ለመጉዳት አስባችሁ የነበረ ቢሆንም አምላክ ግን . . . ነገሩን ለመልካም አደረገው።”