በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ጥር 29, 2021
ሩሲያ

የሩሲያ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በስድስት የይሖዋ ምሥክሮች ላይ የተላለፈው ፍርድ እንዲጸና ወሰነ

የሩሲያ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በስድስት የይሖዋ ምሥክሮች ላይ የተላለፈው ፍርድ እንዲጸና ወሰነ

ጥር 29, 2021 የዩልያኖቭስክ አውራጃ ፍርድ ቤት በወንድም አሌክሳንደር ጃኒን፣ በወንድም ኸረን ኸቺክያን፣ በወንድም አንድሬ ታባኮቭ፣ በወንድም ሚካኼል ዘለንስኪ እንዲሁም በወንድም ሰርጌ ማይሲን እና በባለቤቱ በእህት ናታሊያ ላይ ጥቅምት 2020 የተላለፈው ፍርድ እንዲጸና ወሰነ። ከወንድም ሰርጌ በቀር በሌሎቹ የይሖዋ ምሥክሮች ላይ መጀመሪያ የተፈረደባቸው የእስር ጊዜ በዚያው እንዲጸና ተወስኗል። በወንድም ሰርጌ ላይ መጀመሪያ የተፈረደበት የአራት ዓመት እስራት ግን ወደ አራት ዓመት ተኩል ከፍ እንዲል ፍርድ ቤቱ ወስኗል። እርግጥ በአሁኑ ጊዜ ማናቸውም እስር ቤት አይገቡም።