በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የካቲት 26, 2021
ሩሲያ

የሩሲያ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በወንድም ሬይማን እና በባለቤቱ ላይ የተላለፈው ፍርድ እንዲቀንስ አደረገ

የሩሲያ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በወንድም ሬይማን እና በባለቤቱ ላይ የተላለፈው ፍርድ እንዲቀንስ አደረገ

የኮስትሮማ አውራጃ ፍርድ ቤት የካቲት 26, 2021 በወንድም ሰርጌ ሬይማን እና በባለቤቱ በቫሌሪያ ላይ ጥቅምት 2020 የተላለፈው ውሳኔ እንዲጸድቅ አደረገ። ሆኖም ፍርድ ቤቱ፣ የተፈረደባቸው የእስር ጊዜ እንዲቀነስ አድርጓል። በወንድም ሰርጌ ላይ የተላለፈው የስምንት ዓመት የገደብ እስራት ወደ ሦስት ዓመት፣ የእህት ቫሌሪያ የሰባት ዓመት የገደብ እስር ደግሞ ወደ ሁለት ዓመት ዝቅ እንዲል አድርጓል። እርግጥ በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርዱም።