በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ጥር 25, 2021
ሩሲያ

የሩሲያ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ወንድም ዩሪ ዛሊፓየቭ ጥፋተኛ አይደለም በሚል የተላለፈውን ውሳኔ አጸና

የሩሲያ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ወንድም ዩሪ ዛሊፓየቭ ጥፋተኛ አይደለም በሚል የተላለፈውን ውሳኔ አጸና

የካባርዲኖ ባልካሪያን ሪፑብሊክ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቃቤ ሕጉ ያቀረበውን ይግባኝ ጥር 25, 2021 ውድቅ አደረገ፤ አቃቤ ሕጉ ይግባኝ ያለው ጥቅምት 7, 2020 የተላለፈውን ወንድም ዩሪ ዛሊፓየቭ ጥፋተኛ አይደለም የሚል ውሳኔ ነው። አቃቤ ሕጉ አሁን የተላለፈውንም ውሳኔ ይግባኝ ሊል ይችላል። አሁን ግን ወንድም ዩሪ ዛሊፓየቭ ጥፋተኛ አይደለም የሚለው ውሳኔ ተፈጻሚ ይሆናል። ወንድም ዩሪ ዛሊፓየቭ ከቀረበበት ክስ ሁሉ ነፃ ሆኗል። በተጨማሪም ለቀረበበት የሐሰት ክስ ካሳ የመጠየቅ መብት አለው።

ወንድም ዩሪ ዛሊፓየቭ ጥፋተኛ እንዳልሆነ የተፈረደለት ውሳኔ ሊቀለበስ እንደሚችል ቢያውቅም እንኳ በፍርድ ሂደቱ ወቅት በይሖዋ እንደሚታመንና ደፋር እንደሆነ አሳይቷል። ዩሪ፣ ውሳኔው ከመተላለፉ ጥቂት ቀደም ብሎ አምላክ ሩሲያ ውስጥ በይሖዋ ምሥክሮች ላይ የሚደርሰውን ስደት ጨምሮ ክፋትን ሁሉ በቅርቡ እንደሚያጠፋ ለፍርድ ቤቱ በድፍረት ተናግሯል። እንዲህ ብሏል፦ “የሚሰነዘርብን ጥቃት የቱንም ያህል መሰሪ ቢሆን አሳዳጆቻችን መገንዘብ ያለባቸው አንድ ነገር አለ። አምላክ በምድር ላይ ያለውን ክፋት ሁሉ እንደሚያስወግድ በገባው ቃል ላይ ያለኝን እምነት ሊያዳክሙት አይችሉም። በቅርቡ በምድር ላይ ያሉ የተለያየ ዘር ያላቸው ሰዎች ሁሉ ወንድማማችና እህትማማች መሆናቸውን የሚገነዘቡበት ጊዜ እንደሚመጣ እርግጠኛ ነኝ። ያኔ የሰው ዘሮችን ሊከፋፍል የሚችል ምንም ነገር አይኖርም። መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ በቅርቡ የሚያደርገውን ሲናገር እንዲህ ይላል፦ ‘እነሱ ሰይፋቸውን ማረሻ፣ ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ። አንዱ ብሔር በሌላው ብሔር ላይ ሰይፍ አያነሳም፤ ከእንግዲህ ወዲህ ጦርነት አይማሩም።’—ኢሳይያስ 2:4

“ይህ ተስፋ በቅርቡ እንደሚፈጸም እርግጠኛ ነኝ!”