በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የሩሲያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሕንፃ

ኅዳር 25, 2021
ሩሲያ

የሩሲያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ—በይሖዋ ምሥክሮች ላይ ምን ውጤት ይኖረው ይሆን?

የሩሲያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ—በይሖዋ ምሥክሮች ላይ ምን ውጤት ይኖረው ይሆን?

ጥቅምት 28, 2021 የሩሲያ ጠቅላይ ፍርድ ከጽንፈኝነት እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ በወጣ ሕግ ላይ ማሻሻያ አደረገ። ማሻሻያው በግለሰብም ሆነ በቡድን ደረጃ የሚቀርብ አምልኮ በታገደ ሃይማኖታዊ ድርጅት እንቅስቃሴ እንደመካፈል ተደርጎ ሊቆጠር አንደማይገባ የሚገልጽ ነው። ሆኖም ይህ ውሳኔ በይሖዋ ምሥክሮች ላይ እየደረሰ ያለውን የተቀነባበረ ስደት ማስቆም አልቻለም፤ ምክንያቱም የሩሲያ ባለሥልጣናት ማሻሻያውን የሚተረጉሙበት መንገድ በጣም የተለያየ ነው።

ለምሳሌ ያህል፣ ጥቅምት 28 ማስተካከያው ከተደረገ ወዲህ ባለሥልጣናት ቢያንስ በ13 የይሖዋ ምሥክሮች ቤቶች ላይ ፍተሻ አድርገዋል፣ እህት አይሪና ሎክቪትስካያ ያቀረበችውን የይግባኝ ጥያቄ ውድቅ አድርገዋል እንዲሁም የ80 ዓመት አረጋዊ የሆኑትን እህት የሌና ሳቨልዬቫን ወንጀለኛ ብለው ፈርደውባቸዋል። በተቃራኒው ግን ኅዳር 22, 2021 በቭላዲቮስቶክ ያለ ፍርድ ቤት ወንድም ዲሚትሪ ባርማኪን ጥፋተኛ እንዳልሆነ በመወሰን ከቀረበበት ክስ ሁሉ ነፃ አድርጎታል።

የተደረገው ማሻሻያ ወንድሞቻችንን እየደረሰባቸው ካለው ስደት ሊገላግላቸው አሊያም የእስር ጊዜያቸውን ሊያራዝምባቸው ይችላል፤ ይህን አሁን ላይ ማወቅ አይቻልም። ውጤቱ ምንም ሆነ ምን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን እውነተኛና ዘላቂ መዳን የሚያገኙበት ጊዜ እስኪመጣ ድረስ ይሖዋ በደስታ እንዲጸኑ እንደሚረዳቸው ሙሉ በሙሉ እንተማመናለን።—መዝሙር 146:3-5