ጥቅምት 28, 2020
ሩሲያ
የሩሲያ ፍርድ ቤት በሁለት ወንድሞችና በሁለት እህቶች ላይ የተላለፈውን ውሳኔ ደገፈ
ጥቅምት 28, 2020 የብሪያንስክ ክልላዊ ፍርድ ቤት በቭላዲሚር፣ በኤዱዋርድ፣ በታትያና እና በኦልጋ ላይ የተላለፈውን ውሳኔ ደገፈ። መጀመሪያ ላይ ከአንድ ዓመት እስከ አንድ ዓመት ከሦስት ወር የሚደርስ እስር ተፈርዶባቸው ነበር። ሆኖም ያለፍርድ ታስረው የቆዩበት ጊዜ ስለታሰበላቸው መታሰር አላስፈለጋቸውም። ይህ ብይን እነዚህ ወንድሞችና እህቶች ጥፋተኛ ናቸው ተብሎ የተላለፈውን ውሳኔ ያጸናባቸዋል። ይሁንና ለእስር ባለመዳረጋቸው ደስተኛ ናቸው። አቃቤ ሕጉ ከበድ ያለ ቅጣት እንዲጣልባቸው እንዲጠይቅ የሚፈቅድለት የሕግ አግባብ የለም።
ጉዳያቸው መጀመሪያ በፍርድ ቤት ከመታየቱ በፊት ወንድሞች 316 ቀናት፣ እህቶች ደግሞ 245 ቀናት በእስር ቆይተዋል። ከእስር ከተለቀቁ በኋላ፣ እህቶች በ2020 የበላይ አካሉ ሪፖርት ቁጥር 5 ላይ ቃለ መጠይቅ ተደርጎላቸዋል። ጸሎት፣ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብና የአመስጋኝነት መንፈስ የደረሰባቸውን ስደት በደስታ ለመቋቋም እንደረዳቸው ተናግረዋል።