በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ጥቅምት 8, 2020
ሩሲያ

የሩሲያ ፍርድ ቤት በስድስት የይሖዋ ምሥክሮች ላይ ጥፋተኛ ናቸው የሚል ብይን አስተላለፈ፤ በገደብ እስራት እንዲቀጡም ወስኗል

የሩሲያ ፍርድ ቤት በስድስት የይሖዋ ምሥክሮች ላይ ጥፋተኛ ናቸው የሚል ብይን አስተላለፈ፤ በገደብ እስራት እንዲቀጡም ወስኗል

በዩልያኖቭስክ የሚገኘው የዛስቪያዥስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ጥቅምት 8, 2020 ወንድም አሌክሳንደር ጃኒን፣ ወንድም ኸረን ኸቺክያን፣ ወንድም አንድሬ ታባኮቭ፣ ወንድም ሚካኼል ዘለንስኪ እንዲሁም ወንድም ሰርጌ ማይሲን እና ባለቤቱ እህት ናታሊያ ጥፋተኛ ናቸው የሚል ብይን አስተላልፏል። ፍርድ ቤቱ ከሁለት ዓመት ተኩል እስከ አራት ዓመት በሚደርስ የገደብ እስራት እንዲቀጡ ወስኗል። በመሆኑም ወንድሞቻችንና እህታችን አሁን እስር ቤት ገብተው አይታሰሩም ማለት ነው።