በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ጥር 24, 2020
ሩሲያ

የሩሲያ ፍርድ ቤት በወንድም ማርኪን እና በወንድም ትሮፊሞቭ ላይ የገንዘብ ቅጣት ጣለ። ሆኖም እስራት አልተበየነባቸውም

የሩሲያ ፍርድ ቤት በወንድም ማርኪን እና በወንድም ትሮፊሞቭ ላይ የገንዘብ ቅጣት ጣለ። ሆኖም እስራት አልተበየነባቸውም

ዓርብ፣ ጥር 24, 2020 በሙርማንስክ የሚገኘው የፖሊያርኒ አውራጃ ፍርድ ቤት ወንድም ሮማን ማርኪን እና ወንድም ቪክቶር ትሮፊሞቭ ጥፋተኛ ናቸው የሚል ብያኔ ያስተላለፈ ሲሆን በወንድም ማርኪን ላይ የ300,000 ሩብል (4,858 የአሜሪካ ዶላር) በወንድም ትሮፊሞቭ ላይ ደግሞ የ350,000 ሩብል (5,668 የአሜሪካ ዶላር) የገንዘብ ቅጣት ጥሏል። ወንድሞቻችን ጥፋተኛ ተብለው የተፈረደባቸው መሆኑ ቢያሳዝነንም እስር ቤት ባለመግባታቸው ደስተኞች ነን።