በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የካቲት 24, 2021
ሩሲያ

የሩሲያ ፍርድ ቤት በወንድም ሮማን ባራኖቭስኪ እና በአረጋዊት እናቱ በእህት ቫለንቲና ባራኖቭስካያ ላይ እስራት ፈረደባቸው

የሩሲያ ፍርድ ቤት በወንድም ሮማን ባራኖቭስኪ እና በአረጋዊት እናቱ በእህት ቫለንቲና ባራኖቭስካያ ላይ እስራት ፈረደባቸው

በካካሲያ ሪፑብሊክ የሚገኘው የአባካን ከተማ ፍርድ ቤት የካቲት 24, 2021 በወንድም ሮማን ባራኖቭስኪ ላይ የስድስት ዓመት እስራት ፈርዶበታል። በተጨማሪም የወንድም ሮማን እናት በሆነችው በእህት ቫለንቲና ባራኖቭስካያ ላይ የሁለት ዓመት እስራት ፈርዶባታል። ሩሲያ ውስጥ እህቶቻችን በእምነታቸው ምክንያት እስር ቤት እንዲገቡ ሲደረግ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። እህት ቫለንቲና ሚያዝያ 2021 ላይ 70 ዓመት የሚሞላት ሲሆን በ2020 አንጎሏ ውስጥ ደም ፈስሶ ነበር።

የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ከተሰማ በኋላ ሁለቱም ወደ እስር ቤት ተወስደዋል። ወንድም ሮማንና እናቱ ይህን ውሳኔ አስመልክቶ ይግባኝ ይጠይቃሉ።