ታኅሣሥ 22, 2020
ሩሲያ
የሩሲያ ፍርድ ቤት በወንድም ሲምዮን ባይባክ ላይ የገደብ እስር በየነበት
በሮስቶቭ ኦን ዶን የሚገኘው የሌኒንስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ታኅሣሥ 21, 2020 ወንድም ሲምዮን ባይባክ ጥፋተኛ ነው የሚል ውሳኔ ያሳለፈ ሲሆን በሦስት ዓመት ተኩል የገደብ እስር እንዲቀጣም ወስኗል። እርግጥ ወንድም ሲምዮን እስር ቤት ገብቶ አይታሰርም።
ወንድም ሲምዮን ከጥቂት ቀናት በፊት የመጨረሻ ሐሳቡን ለፍርድ ቤቱ ባቀረበበት ወቅት አንድ ታዋቂ ሩሲያዊ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የተናገረውን ሐሳብ ጠቅሶ ነበር። ይህ ግለሰብ “እነሱ [የይሖዋ ምሥክሮች] ስደት ይደርስባቸዋል፤ ሆኖም ሁልጊዜ ደስተኛ ናቸው” ብሎ ነበር። ከዚያም ወንድም ሲምዮን “ይህ እውነት ነው። እኔ አላዘንኩም ወይም ጥላቻ አላደረብኝም በማለት በእርግጠኝነት ተናግሯል። ከዚያም 2 ቆሮንቶስ 4:8, 9ን አነበበና ይህ ጥቅስ ከእሱም ሆነ በሩሲያ ውስጥ ካሉ ሌሎች የይሖዋ ምሥክሮች ጋር በተያያዘ እንደሚሠራ ተናገረ። ጥቅሱ እንዲህ ይላል፦ “በየአቅጣጫው ብንደቆስም መፈናፈኛ አናጣም፤ ግራ ብንጋባም መውጫ ቀዳዳ አናጣም፤ ስደት ቢደርስብንም አልተተውንም፤ በጭንቀት ብንዋጥም አንጠፋም።”