በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

አሌክሳንደር ሶሎቭየቭ እና አና ሶሎቭየቭ

ሐምሌ 5, 2019
ሩሲያ

የሩሲያ ፍርድ ቤት በወንድም አሌክሳንደር ሶሎቭየቭ ላይ ፈረደ

የሩሲያ ፍርድ ቤት በወንድም አሌክሳንደር ሶሎቭየቭ ላይ ፈረደ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 4, 2019 በፐርም ከተማ የሚገኘው የኦርድዠኒኪድዘፍስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት በወንድም አሌክሳንደር ሶሎቭየቭ ላይ ፍርድ ያስተላለፈ ሲሆን የ300,000 ሩብል (4,731 የአሜሪካ ዶላር) የገንዘብ ቅጣት ጥሎበታል።

ወንድም ሶሎቭየቭ ግንቦት 22, 2018 ምሽት ከባለቤቱ ከአና ጋር ከውጭ አገር ሲመለስ ባቡር ጣቢያ ውስጥ ተይዞ ታሰረ። ፖሊሶች ወንድም ሶሎቭየቭን በካቴና አስረው ወደ ጣቢያ ወስደው አሰሩት። ፖሊሶች እህት አናንም በሌላ መኪና ወስደዋት ነበር። ፖሊሶቹ የእነወንድም ሶሎቭየቭን ቤት ሲፈትሹ ያደሩ ሲሆን ፎቶግራፎችን፣ የኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎችንና መጽሐፍ ቅዱሶችን ወስደዋል።

እህት አና ምርመራ ከተካሄደባት በኋላ ያለ ምንም ክስ ተለቀቀች። ወንድም ሶሎቭየቭ ግን ክስ የተመሠረተበት ከመሆኑም ሌላ ከግንቦት 24 እስከ ኅዳር 19, 2018 በቁም እስር ቆይቷል። ፍርድ ቤት እስኪቀርብ ድረስ በእንቅስቃሴዎቹ ላይ ገደብ ተጥሎበት ነበር።

የወንድም ሶሎቭየቭ ጠበቆች ይግባኝ ይጠይቃሉ። በተጨማሪም ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አግባብ ያልሆነ እስራት አጣሪ ቡድን አቤቱታቸውን አቅርበዋል።

እንደ ሩሲያ ባሉ አገሮች ውስጥ ስደት ቢበረታም ‘በምንም መንገድ በጠላቶቻችን አንሸበርም።’ ይሖዋ፣ ታላቁ የመዳን ቀን እስኪመጣ ድረስ ለመጽናት የሚያስፈልገንን ነገር ለሁላችንም እንደሚሰጠን እንተማመናለን።—ፊልጵስዩስ 1:28