በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የካቲት 3, 2021
ሩሲያ

የሩሲያ ፍርድ ቤት በወንድም አርተር ሎክቪትስኪ ላይ የገደብ እስራት ፈረደበት

የሩሲያ ፍርድ ቤት በወንድም አርተር ሎክቪትስኪ ላይ የገደብ እስራት ፈረደበት

ሩሲያ ውስጥ በአይሁዳውያን ራስ ገዝ ክልል የሚገኘው የቢሮቢድዣን አውራጃ ፍርድ ቤት የካቲት 2, 2021 የ35 ዓመቱ አርተር ሎክቪትስኪ ጥፋተኛ ነው የሚል ውሳኔ አሳለፈ። ፍርድ ቤቱ በወንድም ላይ የሁለት ዓመት ተኩል የገደብ እስራት በይኗል፤ እንዲሁም ለሦስት ዓመት ያህል ክትትል እንዲደረግበት ወስኗል። እርግጥ ወንድም አርተር ሎክቪትስኪ በአሁኑ ወቅት እስር ቤት ገብቶ አይታሰርም።

አርተር ለፍርድ ቤቱ በተናገረው የመጨረሻ ሐሳብ ላይ እንዲህ ብሏል፦ “ውጤቱ ምንም ይሁን ምን በዚህ የፍርድ ሂደት ውስጥ ማለፍ መቻሌን እንደ ትልቅ መብት እቆጥረዋለሁ። ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረው ቃል አሁንም ፍጻሜውን ሲያገኝ እያየሁ ነው። ኢየሱስ የተናገረው ሐሳብ የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ በሆነው በማርቆስ ምዕራፍ 13 ቁጥር 9 እና 10 ላይ ይገኛል፤ እንዲህ ይላል፦ ‘እናንተ ግን ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። ሰዎች ለፍርድ ሸንጎዎች አሳልፈው ይሰጧችኋል፤ . . . በዚያ ጊዜ ለእነሱ መመሥከር ትችላላችሁ። አስቀድሞም ምሥራቹ ለብሔራት ሁሉ መሰበክ አለበት።’ . . . ይህን ማወቄ ስለ አምላክ ዓላማ ለሌሎች እንድናገር ያነሳሳኛል። ክቡር ዳኛ፣ ይህን ለእርስዎም መናገር በመቻሌ ታላቅ ክብር ይሰማኛል።”