በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም አናቶሊ ቶካሬቭ ከፍርድ ቤቱ ውጭ ቆሞ፣ ነሐሴ 2020

ጥቅምት 23, 2020
ሩሲያ

የሩሲያ ፍርድ ቤት በወንድም አናቶሊ ቶካሬቭ ላይ የገንዘብ ቅጣት ጣለበት

የሩሲያ ፍርድ ቤት በወንድም አናቶሊ ቶካሬቭ ላይ የገንዘብ ቅጣት ጣለበት

ወቅታዊ መረጃ | የሩሲያ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የቀረበለትን ይግባኝ ውድቅ አደረገ

ኅዳር 30, 2021 ስድስተኛው ጠቅላይ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ወንድም አናቶሊ ቶካሬቭ ያቀረበውን ይግባኝ ውድቅ አደረገ። በመሆኑም መጀመሪያ ላይ የተጣለበትን የገንዘብ ቅጣት መክፈል ይጠበቅበታል።

በኪሮቭ የሚገኘው የኦክትያብርስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ጥቅምት 23, 2020 ወንድም አናቶሊ ጥፋተኛ ነው የሚል ውሳኔ አስተላልፏል፤ በተጨማሪም 500,000 ሩብል (6,552 የአሜሪካ ዶላር) እንዲቀጣ ወስኗል። ወንድም አናቶሊ በአሥር ቀን ውስጥ ይግባኝ መጠየቅ ይችላል።

ወንድም አናቶሊ ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው የመከላከያ ሐሳብ መጨረሻ ላይ እንዲህ በማለት በድፍረት ተናግሯል፦ “በዚህ የወንጀል ክስ ሂደት ሕግ አስከባሪ ባለሥልጣናት ‘እምነትህን ካድ፤ አሻፈረኝ ካልክ ግን በይፋ ከባድ ቅጣት ትቀጣለህ’ ያሉኝ ያህል ተሰምቶኛል። . . . ክቡር ዳኛ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት ስቀርብ የተናገርኩትን ነገር አሁንም በድጋሚ መናገር እፈልጋለሁ። በአምላክ ላይ ያለኝን እምነት አልክድም። . . . እርግጥ እንደምታሰር ወይም እንደምገደል የሚደርስብኝ ዛቻ እንደ ማንኛውም የይሖዋ ምሥክር ያስፈራኛል፤ ጽንፈኛ ተብዬ መፈረጄ ደግሞ ስሜ ያለአግባብ እንዲጎድፍ ያደርጋል። ሆኖም ክቡር ዳኛ፣ አምላኬን በመካድ የእሱን ፍቅር ማጣት ፈጽሞ አልፈልግም።”