በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ካሳን ኮገት እና ባለቤቱ ዬካተሪና ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ በኋላ

መስከረም 10, 2020
ሩሲያ

የሩሲያ ፍርድ ቤት በወንድም ካሳን ኮገት ላይ ፈረደበት

የሩሲያ ፍርድ ቤት በወንድም ካሳን ኮገት ላይ ፈረደበት

በኬሜሮቮ ግዛት የሚገኘው የቤሬዞቭስኪ ከተማ ፍርድ ቤት መስከረም 10, 2020 በወንድም ካሳን ኮገት ላይ ፈረደበት። ፍርድ ቤቱ በወንድም ላይ የሁለት ዓመት ተኩል እስር በገደብ ፈርዶበታል። ከዚህም ሌላ ፍርድ ቤቱ ወንድም ኮገት ለሁለት ተጨማሪ ዓመታት ገደብ ተጥሎበት እንዲቆይ ወስኗል። ወንድም ካሳን ኮገት ከሚስቱና ከስምንት ዓመት ልጁ ተነጥሎ እስር ቤት እንዲቆይ ባለመወሰኑ ተደስቷል።