በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

መስከረም 25, 2020
ሩሲያ

የሩሲያ ፍርድ ቤት በወንድም ኮንስታንቲን ባዠኖቭ፣ በባለቤቱ እና በአንዲት የ73 ዓመት አረጋዊት እህት ላይ የሁለት ዓመት የገደብ እስራት ፈረደባቸው

የሩሲያ ፍርድ ቤት በወንድም ኮንስታንቲን ባዠኖቭ፣ በባለቤቱ እና በአንዲት የ73 ዓመት አረጋዊት እህት ላይ የሁለት ዓመት የገደብ እስራት ፈረደባቸው

በካምቻትካ ክልል የሚገኘው የየሊዞቭስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ወንድም ኮንስታንቲን ባዠኖቭ፣ ባለቤቱ ስኔዣ እንዲሁም እህት ቬራ ዞሎቶቫ ጥፋተኛ ናቸው የሚል ውሳኔ መስከረም 25, 2020 አስተላለፈ። አቃቤ ሕጉ ወንድም ኮንስታንቲንና ባለቤቱ 600,000 ሩብል (7,850 የአሜሪካ ዶላር) እህት ቬራ ደግሞ 400,000 ሩብል (5,235 የአሜሪካ ዶላር) እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱን ጠይቆ ነበር። ሆኖም ፍርድ ቤቱ የሁለት ዓመት የገደብ እስራት የፈረደባቸው ሲሆን ከዚያ በኋላ ለስድስት ወራት አንዳንድ እገዳዎች እንዲጣሉባቸው ወስኗል። ወንድም ባዠኖቭና ባለቤቱ እንዲሁም እህት ቬራ እስር ቤት የማይገቡና የገንዘብ ቅጣት የማይከፍሉ መሆኑን ማወቃቸው አስደስቷቸዋል።