በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ታኅሣሥ 16, 2020
ሩሲያ

የሩሲያ ፍርድ ቤት በወንድም ዩሪ ሳቨላየቭ ላይ የስድስት ዓመት እስር ፈረደበት

የሩሲያ ፍርድ ቤት በወንድም ዩሪ ሳቨላየቭ ላይ የስድስት ዓመት እስር ፈረደበት

በኖቮስብሪስክ የሚገኘው የሌኒንስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ታኅሣሥ 16, 2020 በወንድም ዩሪ ሳቨላየቭ ላይ የስድስት ዓመት እስር ፈረደበት። ውዱ ወንድማችን ዩሪ ጽኑ አቋሙን እንደጠበቀ ሲሆን የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶችን ማጥናቱ ድፍረት እንዲያገኝ ረድቶታል።

ወንድም ዩሪ ታኅሣሥ 9 በፍርድ ቤቱ ውስጥ የመጨረሻ ሐሳቡን ሲያቀርብ አጋጣሚውን ምሥክርነት ለመስጠት ተጠቅሞበታል። እዚያ በተገኙ ሰዎች ሁሉ ፊት በድፍረት እንዲህ ብሏል፦ “ኢየሱስ የተናገረው አንድ ትንቢት እዚህ በተገኛችሁት ሰዎች ሁሉ ፊት እየተፈጸመ ነው። ትንቢቱ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በማርቆስ 13:9 ላይ ተመዝግቦ ይገኛል። እንዲህ ይላል፦ ‘እናንተ ግን ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። ሰዎች ለፍርድ ሸንጎዎች አሳልፈው ይሰጧችኋል፤ በምኩራብም ትገረፋላችሁ፤ በእኔ ምክንያት በገዢዎችና በነገሥታት ፊት ያቀርቧችኋል፤ በዚያ ጊዜ ለእነሱ መመሥከር ትችላላችሁ።’”