በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የካቲት 14, 2020
ሩሲያ

የሩሲያ ፍርድ ቤት በወንድም ፖፖቭ እና በባለቤቱ ላይ የገንዘብ ቅጣት ጣለባቸው

የሩሲያ ፍርድ ቤት በወንድም ፖፖቭ እና በባለቤቱ ላይ የገንዘብ ቅጣት ጣለባቸው

የቪልዩቺንስክ ከተማ ፍርድ ቤት የካቲት 14, 2020 ወንድም ሚሃይል ፖፖቭ እና ባለቤቱ እህት የሌና ፖፖቫ ጥፋተኛ ናቸው የሚል ፍርድ አስተላለፈ። ፍርድ ቤቱ ወንድም ሚሃይል 350,000 ሩብል (5,508 የአሜሪካ ዶላር) እህት የሌና ደግሞ 300,000 ሩብል (4,722 የአሜሪካ ዶላር) እንዲቀጡ ወስኗል፤ ሆኖም እስራት አልተበየነባቸውም። ሁለቱም ይግባኝ እንደሚጠይቁ ታውቋል።

ሚሃይል እና የሌና የታሰሩት ሐምሌ 2018 ነው። ከዚያ ብዙም ሳይቆይ ግን ተለቅቀው ፍርዳቸውን እንዲጠባበቁ ተወሰነ።

ከ2019 አንስቶ የሩሲያ ፍርድ ቤቶች በ28 የይሖዋ ምሥክሮች ላይ በእምነታቸው የተነሳ ፍርድ አስተላልፈዋል። ከእነዚህ ወንድሞችና እህቶች መካከል አሥሩ የተፈረደባቸው ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ ነው። ሆኖም እነዚህ አሥር ወንድሞችና እህቶች እስካሁን እስር ቤት አልገቡም።