ግንቦት 31, 2021
ሩሲያ
የሩሲያ ፍርድ ቤት አራት የይሖዋ ምሥክሮች ያቀረቡትን ይግባኝ ውድቅ አደረገ
ግንቦት 28, 2021 የኦምስክ ክልላዊ ፍርድ ቤት ወንድም ሰርጌ ፖልያኮቭ እና ባለቤቱ አነስቴዥያ እንዲሁም እህት ጋውካር ቤክቴሚሮቫ እና እህት ዲናራ ዲዩስኬየቫ ያቀረቡትን ይግባኝ ውድቅ አድርጓል። በመሆኑም ወንድም ሰርጌ እስር ቤት ይቆያል። በሦስቱ እህቶች ላይ የተላለፈው የገደብ እስራትም በዚያው ይጸናል።