በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የካቲት 15, 2021
ሩሲያ

የሩሲያ ፍርድ ቤት እህት ስቬትላና ሞኒስ በእምነቷ ምክንያት በገንዘብ እንድትቀጣ ወሰነ

የሩሲያ ፍርድ ቤት እህት ስቬትላና ሞኒስ በእምነቷ ምክንያት በገንዘብ እንድትቀጣ ወሰነ

ሩሲያ ውስጥ በአይሁዳውያን ራስ ገዝ ክልል የሚገኘው የቢሮቢድዣን አውራጃ ፍርድ ቤት የካቲት 15, 2021 እህት ስቬትላና ሞኒስ በሕግ የታገደ ድርጅት በሚያደርገው እንቅስቃሴ በመሳተፍ ጥፋተኛ ሆና ተገኝታለች የሚል ውሳኔ አሳልፏል። ፍርድ ቤቱ 10,000 ሩብል (137 የአሜሪካ ዶላር) እንድትቀጣ ወስኗል።

ስቬትላና ለፍርድ ቤቱ በተናገረችው የመጨረሻ ሐሳብ ላይ እምነት እና ድፍረት እንዳላት አሳይታለች። እንዲህ ብላለች፦ “እዚህ ፊታችሁ የቆምኩት . . . በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስና በአባቱ በይሖዋ አምላክ ስም የተነሳ እንደሆነ ለፍርድ ቤቱ መናገር እፈልጋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስም ስለዚህ ጉዳይ ይናገራል። አንደኛ ጴጥሮስ 4:14-16 እንዲህ ይላል፦ ‘ለክርስቶስ ስም ስትሉ ብትነቀፉ ደስተኞች ናችሁ፤ ምክንያቱም የክብር መንፈስ ይኸውም የአምላክ መንፈስ በእናንተ ላይ ያርፋል። ይሁን እንጂ ከእናንተ መካከል ማንም ነፍሰ ገዳይ ወይም ሌባ ወይም ክፉ አድራጊ ወይም በሌሎች ሰዎች ጉዳይ ጣልቃ የሚገባ ሆኖ መከራ አይቀበል። ይሁንና ማንም ሰው ክርስቲያን በመሆኑ መከራ ቢደርስበት ምንም ኀፍረት አይሰማው፤ ይልቁንም ይህን ስም ተሸክሞ አምላክን ያክብር።’”