በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ሚያዝያ 22, 2021
ሩሲያ

የሩሲያ ፍርድ ቤት እህት የሌና ረይኖ-ቸርኒሾቫ ያቀረበችውን ይግባኝ ውድቅ አደረገ

የሩሲያ ፍርድ ቤት እህት የሌና ረይኖ-ቸርኒሾቫ ያቀረበችውን ይግባኝ ውድቅ አደረገ

ሚያዝያ 22, 2021 ሩሲያ የሚገኘው የአይሁዳውያን ራስ ገዝ ክልል ፍርድ ቤት እህት የሌና ረይኖ-ቸርኒሾቫ ያቀረበችውን ይግባኝ ውድቅ አድርጓል። እንዲያውም አቃቤ ሕግ ቅጣቱ እንዲከብድባት ያቀረበውን ይግባኝ በመቀበል በእህት የሌና ላይ መጀመሪያ የተላለፈው የ10,000 ሩብል (135 የአሜሪካ ዶላር) ቅጣት ወደ ሁለት ዓመት ተኩል የገደብ እስራት እንዲቀየር ወስኗል። እርግጥ እህት የሌና አሁን ወህኒ አትወርድም።