በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የካቲት 16, 2021
ሩሲያ

የሩሲያ ፍርድ ቤት እህት ዩሊያ ካጋኖቪች በገንዘብ እንድትቀጣ ወሰነ

የሩሲያ ፍርድ ቤት እህት ዩሊያ ካጋኖቪች በገንዘብ እንድትቀጣ ወሰነ

ሩሲያ ውስጥ በአይሁዳውያን ራስ ገዝ ክልል የሚገኘው የቢሮቢድዣን አውራጃ ፍርድ ቤት የካቲት 16, 2021 እህት ዩሊያ ካጋኖቪች “ጽንፈኛ ድርጅት በሚያከናውነው እንቅስቃሴ በመካፈል” ጥፋተኛ ሆና ተገኝታለች የሚል ውሳኔ አሳልፏል። ፍርድ ቤቱ እህት ዩሊያ ካጋኖቪች 10,000 ሩብል (135 የአሜሪካ ዶላር) እንድትቀጣ ወስኗል።