በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ግንቦት 13, 2021
ሩሲያ

የሩሲያ ፍርድ ቤት እህት ዩሊያ ካጋኖቪች ያቀረበችውን ይግባኝ ውድቅ አደረገ

የሩሲያ ፍርድ ቤት እህት ዩሊያ ካጋኖቪች ያቀረበችውን ይግባኝ ውድቅ አደረገ

ግንቦት 13, 2021 ሩሲያ ውስጥ የሚገኘው የአይሁዳውያን ራስ ገዝ ክልል ፍርድ ቤት እህት ዩሊያ ካጋኖቪች ያቀረበችውን ይግባኝ ውድቅ አደረገ። በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ አቃቤ ሕግ ያቀረበውን ጥያቄ በመቀበል በእህት ዩሊያ ላይ መጀመሪያ የተጣለባት የ10,000 ሩብል (135 የአሜሪካ ዶላር) መቀጫ ወደ ሁለት ዓመት ተኩል የገደብ እስር እንዲቀየር ወስኗል። እርግጥ እህት ሞኒስ አሁን ወህኒ አትወርድም።