በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ጥር 26, 2021
ሩሲያ

የሩሲያ ፍርድ ቤት እህት ገሊና ፓርኮቫ በገደብ እስራት እንድትቀጣ ወሰነ

የሩሲያ ፍርድ ቤት እህት ገሊና ፓርኮቫ በገደብ እስራት እንድትቀጣ ወሰነ

በሮስቶቭ-ኦን-ዶን ከተማ የሚገኘው የሌኒንስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ጥር 26, 2021 እህት ገሊና ፓርኮቫ ጥፋተኛ ናት የሚል ውሳኔ ያሳለፈ ሲሆን በሁለት ዓመት ከሦስት ወር የገደብ እስራት እንድትቀጣ ወስኗል። እርግጥ አሁን እስር ቤት አትገባም።

እህት ገሊና ፓርኮቫ ለፍርድ ቤቱ በሰጠችው የመጨረሻ ሐሳብ ላይ እንዲህ ስትል በድፍረት ተናግራለች፦ “የእምነት ሰው እንደመሆኔ መጠን በዛሬው ጊዜ እንዲህ ያለ ችግር የሚደርስብኝ ለምን እንደሆነ አውቃለሁ። ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ተናግሯል። በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 15 ቁጥር 20 ላይ ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፦ ‘ባሪያ ከጌታው አይበልጥም ብዬ የነገርኳችሁን ቃል አስታውሱ። እኔን ስደት አድርሰውብኝ ከሆነ እናንተንም ስደት ያደርሱባችኋል።’

“በሽተኞችን የፈወሰውን፣ የተራቡትን የመገበውን፣ ስለ አባቱና ወደፊት ስለሚመጣው መንግሥት ያስተማረውን ኢየሱስን እንዲህ ያለ ስደት ካደረሱበት ተከታዮቹ ከዚህ የተለየ ነገር ሊጠብቁ ይችላሉ? በእምነቴ ምክንያት እንዲህ ያለ ስደት እየደረሰብኝ መሆኑ በራሱ በትክክለኛው መንገድ ላይ እየተጓዝኩ እንዳለሁ ይበልጥ እርግጠኛ እንድሆን አድርጎኛል!”