ጥር 19, 2021
ሩሲያ
የሩሲያ ፍርድ ቤት ወንድም ሰርጌ ለደንዮቭ ያቀረበውን የይግባኝ ጥያቄ ውድቅ አደረገ
ጥር 19, 2021 የካምቻትካ ክልላዊ ፍርድ ቤት ወንድም ሰርጌ ለደንዮቭ ያቀረበውን የይግባኝ ጥያቄ ውድቅ አደረገ። በዚህም ምክንያት መጀመሪያ ላይ የተፈረደበት የሁለት ዓመት የገደብ እስር ይጸናል። እርግጥ እስር ቤት ገብቶ አይታሰርም።
የይግባኝ ጥያቄው ውድቅ ከመደረጉ በፊት ወንድም ሰርጌ ለደንዮቭ ለፍርድ ቤቱ ሐሳቡን የመግለጽ አጋጣሚ አግኝቶ ነበር። ስለ እምነቱ በድፍረት የተናገረ ሲሆን ይሖዋን ማምለኩን እንደሚቀጥል በቆራጥነት ተናግሯል። እንዲህ ብሏል፦ “እምነቴ የተመሠረተው በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንጂ የትኛውም ድርጅት ባወጣው ደንብ ላይ አይደለም። ‘እያንዳንዱ ቤት ሠሪ እንዳለው የታወቀ ነው፤ ሁሉን ነገር የሠራው ግን አምላክ ነው’፤ ይህ አምላክ ደግሞ ‘ስሙ ይሖዋ ነው።’ (ዕብራውያን 3:4፤ ዘፀአት 15:3) የሚፈረድብኝ የትኛውም ዓይነት ፍርድ ይህን ሐሳብ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥም ሆነ ከልቤ ውስጥ ሊያጠፋው አይችልም።”