በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የሩሲያ ፍርድ ቤት ወንድም አሌክሲ መትስገር እምነቱን በማራመዱ ምክንያት ጥፋተኛ ነው የሚል ብይን አስተላልፏል፤ እንዲሁም በገንዘብ እንዲቀጣ ወስኗል

ኅዳር 21, 2019
ሩሲያ

የሩሲያ ፍርድ ቤት ወንድም አሌክሲ መትስገር 350,000 ሩብል እንዲቀጣ ወሰነ፤ አቃቤ ሕግ ወንድም የሦስት ዓመት እስራት እንዲበየንበት ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ ተደረገ

የሩሲያ ፍርድ ቤት ወንድም አሌክሲ መትስገር 350,000 ሩብል እንዲቀጣ ወሰነ፤ አቃቤ ሕግ ወንድም የሦስት ዓመት እስራት እንዲበየንበት ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ ተደረገ

ኅዳር 14, 2019 በፐርም የሚገኘው የኦርድዠኒኪድዘፍስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ወንድም አሌክሲ መትስገር ጥፋተኛ ነው የሚል ብይን አስተላልፏል፤ በተጨማሪም ወንድም 350,000 ሩብል (5,460 የአሜሪካ ዶላር ገደማ) እንዲቀጣ ወስኗል። ወንድም መትስገር ጽንፈኛ ተብለው በዚህ ዓመት በሩሲያ ከተፈረደባቸው 12 ወንድሞች መካከል አንዱ ሆኗል። ወንድም መትስገር የተፈረደበት የሚያምንበትን ነገር ሰላማዊ በሆነ መንገድ በማራመዱና ለሌሎች በማካፈሉ ምክንያት ነው። የወንድም መትስገር ጠበቃ ይግባኝ እንደሚል አሳውቋል።

ሚያዝያ 25, 2019፣ ወንድም መትስገር የይሖዋ ምሥክር በመሆኑ ብቻ የወንጀል ክስ ተመሥርቶበታል። ከቀረቡት ማስረጃዎች መካከል ከወንድም መትስገር ጋር ያደረጉትን ሃይማኖታዊ ውይይት በድብቅ የቀዱ ሰዎች ያቀረቡት ቅጂ ይገኝበታል።

ክሱ መሰማት የጀመረው ጥቅምት 14, 2019 ነው። የከተማው አቃቤ ሕግ ወንድም መትስገር በሦስት ዓመት እስራት እንዲቀጣ ጠይቆ ነበር። ፍርድ ቤቱ ወንድም መትስገር እንዲታሰር ባይወስንም ጥፋተኛ ነው ተብሎ መፈረጁ አሳስቦናል፤ ምክንያቱም ይህ አካሄድ በዚህ ከቀጠለ ሌሎች ወንድሞችና እህቶችም በእምነታቸው ምክንያት ብቻ ሊፈረድባቸው ይችላል።

የሩሲያ ባለሥልጣናት በወንድሞቻችን ላይ ያለምክንያት ስደት ቢያደርሱባቸውም ይሖዋ ወንድሞችን ማበረታታቱንና ማጠናከሩን እንደሚቀጥል እርግጠኞች ነን።—መዝሙር 119:76, 161