በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የካቲት 26, 2021
ሩሲያ

የሩሲያ ፍርድ ቤት ወንድም አሌክሲ ሚረትስኪ የእስር ጊዜውን ሳይጨርስ እንዲለቀቅ የቀረበውን ጥያቄ ውድቅ አደረገ

የሩሲያ ፍርድ ቤት ወንድም አሌክሲ ሚረትስኪ የእስር ጊዜውን ሳይጨርስ እንዲለቀቅ የቀረበውን ጥያቄ ውድቅ አደረገ

የካቲት 26, 2021 የኦረንበርግ ማዕከላዊ አውራጃ ፍርድ ቤት ወንድም አሌክሲ ሚረትስኪ የእስር ጊዜውን ሳይጨርስ እንዲለቀቅ የቀረበውን ይግባኝ ውድቅ አደረገ። ወንድም አሌክሲ የካቲት 2020 እስር ቤት ውስጥ ከተደበደቡት አምስት ወንድሞች መካከል አንዱ ነው። ወንድም አሌክሲ ከግማሽ በላይ የሚሆነውን የእስር ጊዜውን አጠናቅቋል።