በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ሚያዝያ 15, 2021
ሩሲያ

የሩሲያ ፍርድ ቤት ወንድም አሌክሳንደር ኢቨሺን ያቀረበውን ይግባኝ ውድቅ አደረገ

የሩሲያ ፍርድ ቤት ወንድም አሌክሳንደር ኢቨሺን ያቀረበውን ይግባኝ ውድቅ አደረገ

ሚያዝያ 15, 2021 የክራስኖዳር የክልል ፍርድ ቤት በወንድም አሌክሳንደር ኢቨሺን ላይ የተላለፈው የሰባት ዓመት ተኩል እስራት እንዲጸና ወሰነ። በመሆኑም ወንድም አሌክሳንደር እስር ቤት ይቆያል። ይህ ብያኔ ድርጅቱ በ2017 ከታገደበት ጊዜ አንስቶ በይሖዋ ምሥክሮች ላይ የተላለፈው ከባዱ ፍርድ ነው።