በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የካቲት 12, 2021
ሩሲያ

የሩሲያ ፍርድ ቤት ወንድም ኢጎር ሰሬቭ ጥፋተኛ ነው በማለት በገደብ እስራት እንዲቀጣ ወሰነ

የሩሲያ ፍርድ ቤት ወንድም ኢጎር ሰሬቭ ጥፋተኛ ነው በማለት በገደብ እስራት እንዲቀጣ ወሰነ

ሚያዝያ 29, 2021 የአይሁዳውያን ራስ ገዝ ክልል ፍርድ ቤት ወንድም ኢጎር ጥፋተኛ ነው የሚለው ውሳኔና የተላለፈበት የሁለት ዓመት ተኩል እስራት ፍርድ እንዲጸና ወሰነ።

በአይሁዳውያን ራስ ገዝ ክልል የሚገኘው የቢሮቢድዣን አውራጃ ፍርድ ቤት የካቲት 12, 2021 ኢጎር ጥፋተኛ ነው በሚል የሁለት ዓመት ተኩል የገደብ እስራት በይኖበታል።

ኢጎር በታማኝነት የጸና ሲሆን በክስ ሂደቱ ወቅት ሁሉ አዎንታዊ አመለካከት ይዞ ቆይቷል። የካቲት 11, 2021 ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው የመጨረሻ ሐሳብ ላይ እንዲህ ብሏል፦ “ለፍርድ ቤቱ የመጨረሻ ሐሳቤን ሳቀርብ እንዴት ብዬ ነው የምጀምረው የሚለውን ጉዳይ ሳስብበት ነበር፤ በኋላም ሐዋርያው ጳውሎስ ለሁሉም ክርስቲያኖች የሰጠውን ምክር ተግባራዊ ባደርግ የተሻለ ነው ብዬ ወሰንኩ። ጳውሎስ ለቆላስይስ ክርስቲያኖች በጻፈው ደብዳቤ ላይ ‘አመስጋኝ መሆናችሁን አሳዩ’ የሚል ማሳሰቢያ ሰጥቶ ነበር።

“ስለዚህ ክቡር ዳኛ፣ በፍርድ ሂደቱ ወቅት ለነበረው ሰላማዊ ሁኔታና ትኩረት ሰጥተው ስላዳመጡን ላመሰግንዎት እፈልጋለሁ። . . . ከሁሉ ይበልጥ ግን ፈጣሪያችን የሆነውን ይሖዋ አምላክን ማመስገን እፈልጋለሁ፤ ምክንያቱም በዚህ የፍርድ ሂደት ወቅት ሁሉ ሲደግፈኝ ነበር። እንዲሁም እንድረጋጋና ውስጣዊ ሰላም እንዲኖረኝ ረድቶኛል።”—ቆላስይስ 3:15