በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ሚያዝያ 1, 2020
ሩሲያ

የሩሲያ ፍርድ ቤት ወንድም ኢጎር ኢቫሺን ጥፋተኛ ነው በማለት የስድስት ዓመት እስር በገደብ በየነበት

የሩሲያ ፍርድ ቤት ወንድም ኢጎር ኢቫሺን ጥፋተኛ ነው በማለት የስድስት ዓመት እስር በገደብ በየነበት

በሳኻ ሪፑብሊክ የሚገኘው የሌንስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት በወንድም ኢጎር ኢቫሺን ላይ በእምነቱ ምክንያት የስድስት ዓመት እስር በገደብ ፈረደበት። ፍርዱ ከተላለፈ በኋላ ወንድም ኢጎር ወደ ቤቱ መመለስ የቻለ ቢሆንም በገደብ የሚቆይበት ጊዜ እስኪያበቃ ድረስ ከእምነቱ እና ከአምልኮው ጋር በተያያዘ የወጡትን ሕጎች ተላልፎ ቢገኝ ወዲያውኑ እስር ቤት ሊገባ ይችላል። ወንድም ኢጎር የተላለፈበትን ፍርድ አስመልክቶ ይግባኝ ይጠይቃል።