በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የካቲት 4, 2020
ሩሲያ

የሩሲያ ፍርድ ቤት ወንድም ኪም እና ወንድም ፖለቮዶቭ ጥፋተኛ ናቸው ብሎ በየነ

የሩሲያ ፍርድ ቤት ወንድም ኪም እና ወንድም ፖለቮዶቭ ጥፋተኛ ናቸው ብሎ በየነ

የካቲት 4, 2020 የካባረቭስክ ከተማ የዢለዝናዳሮዥኒይ ፍርድ ቤት ወንድም ስታኒስላቭ ኪም እና ወንድም ኒኮላይ ፖለቮዶቭ ጥፋተኛ ናቸው ብሎ በመወሰን የሁለት ዓመት እስር በገደብ በይኖባቸዋል። እስር ቤት ባይገቡም ለሁለት ዓመት ያህል በአመክሮ ይቆያሉ። ወንድሞች ውሳኔው እንዲቀየር ይግባኝ ለመጠየቅ አስበዋል። ሁለቱም ወንድሞች ከዚህ ክስ በተጨማሪ ሌላ ክስ የተመሠረተባቸው ሲሆን ጉዳያቸው በዚያው ከተማ በሚገኘው ኢንደስትሪያል አውራጃ ፍርድ ቤት እየታየ ነው። ፍርድ ቤቱ ለሁለተኛው ክስ ብያኔ ገና ቀጠሮ አልሰጠም።