በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ታኅሣሥ 23, 2020
ሩሲያ

የሩሲያ ፍርድ ቤት ወንድም ካሳን ኮገት ያቀረበውን ይግባኝ ውድቅ አደረገ

የሩሲያ ፍርድ ቤት ወንድም ካሳን ኮገት ያቀረበውን ይግባኝ ውድቅ አደረገ

ታኅሣሥ 23, 2020 የኬሜሮቮ ክልል ፍርድ ቤት፣ ወንድም ካሳን ኮገት ያቀረበውን ይግባኝ ውድቅ አደረገ። በመሆኑም በወንድም ካሳን ኮገት ላይ መጀመሪያ የተፈረደበት የሁለት ዓመት ተኩል የገደብ እስር ተፈጻሚ ይሆናል። እርግጥ ወንድም ካሳን ኮገት እስር ቤት ገብቶ አይታሰርም።

ወንድም ካሳን ኮገት የተላለፈበት ፍርድ ጥቁር መዝገብ ላይ እንዲሰፍር የሚያደርገው ቢሆንም ንጹሕ አቋሙን እንደጠበቀና የይሖዋን ሞገስ እንዳገኘ ማወቁ አጽናንቶታል። ወንድም ካሳን ኮገት፣ ባለቤቱ ዬካተሪና እንዲሁም የስምንት ዓመቱ ልጃቸው ቲሞፊ ይሖዋን ማገልገላቸውን ለመቀጠል ቁርጥ ውሳኔ አድርገዋል።

ወንድም ካሳን ኮገት መስከረም 10, 2020 ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው የመጨረሻ ሐሳብ ላይ በድፍረት እንዲህ ብሎ ነበር፦ “በይሖዋ አምላክ ላይ ያለኝን እምነት አልክድም፤ ይህን እንዳደርግ የሚደረግብኝን ማንኛውም ግፊት እንደ ወንጀል ነው የምመለከተው! ይህ ከልቤ የማምንበት ነገር ነው። ማንኛውም ነገር ማለትም ‘ሞትም ቢሆን፣ ሕይወትም ቢሆን፣ መላእክትም ቢሆኑ፣ መንግሥታትም ቢሆኑ፣ አሁን ያሉት ነገሮችም ቢሆኑ፣ ወደፊት የሚመጡት ነገሮችም ቢሆኑ፣ ማንኛውም ኃይል ቢሆን፣ ከፍታም ቢሆን፣ ዝቅታም ቢሆን፣ ሌላ ማንኛውም ፍጥረት ቢሆን ከአምላክ ፍቅር ሊለየን አይችልም።’”—ሮም 8:38, 39