በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ዩሪ ዛሊፓየቭ ፍርድ ቤት ውስጥ የመደምደሚያ ሐሳቡን ሲያቀርብ

ጥቅምት 7, 2020
ሩሲያ

የሩሲያ ፍርድ ቤት ወንድም ዩሪ ዛሊፓየቭ ጥፋተኛ አይደለም አለ!

የሩሲያ ፍርድ ቤት ወንድም ዩሪ ዛሊፓየቭ ጥፋተኛ አይደለም አለ!

በካባርዲኖ ባልካሪያን ሪፑብሊክ የሚገኘው የማይስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ጥቅምት 7, 2020 ወንድም ዩሪ ዛሊፓየቭ ጥፋተኛ አይደለም የሚል ውሳኔ አስተላልፏል፤ በተጨማሪም ወንድም ዩሪን ከቀረበበት ክስ ሁሉ ነፃ አድርጎታል። አቃቤ ሕጉ እስከ አሥር ቀን ድረስ ይግባኝ መጠየቅ ይችላል።

አቃቤ ሕጉ ወንድም ዩሪ ዛሊፓየቭ ሌሎችን ለዓመፅ አነሳስቷል የሚል ክስ አቅርቦ ነበር። ሆኖም ወንድም ዩሪ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያነቡ እንዲሁም ለሌሎች ፍቅርና ደግነት እንዲያሳዩ ከማበረታታት ውጭ ምንም የሠራው ጥፋት እንደሌለ ከ30 የሚበልጡ ሰዎች መሥክረዋል።

ፍርድ ቤቱ ወንድም ዩሪ “ጥፋተኛ አይደለም” የሚል ውሳኔ እንዲያስተላልፍ ምክንያት ከሆኑት ነገሮች አንዱ በተባበሩት መንግሥታት ሥር የሚገኘውና ያለፍርድ እንዲታሰሩ በተደረጉ ሰዎች ዙሪያ የሚሠራው ቡድን የይሖዋ ምሥክሮች በምንም መልኩ ዓመፅ አይፈጽሙም እንዲሁም ሌሎችን ለዓመፅ አያነሳሱም የሚል መደምደሚያ ላይ መድረሱ ነው።

ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ካሳወቀ በኋላ ወንድም ዩሪ እንዲህ ብሏል፦ “ቤተሰቦቼና ጓደኞቼ ሁሉ ይፈረድበታል የሚል ስጋት አድሮባቸው ነበር። ሆኖም ለይሖዋ ምስጋና ይግባውና በፍርድ ሂደቱ ወቅት ከልክ በላይ አልተጨነቅኩም። ንጹሕ ሰው መሆኔን ለማረጋገጥ አስተዋጽኦ ያደረጉትን በሙሉ ከልብ ማመስገን እፈልጋለሁ።”