በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ሐምሌ 28, 2020
ሩሲያ

የሩሲያ ፍርድ ቤት ወንድም ዬቭጌኒ ስፒሪን ከ6,900 የአሜሪካ ዶላር በላይ እንዲቀጣ ወሰነ

የሩሲያ ፍርድ ቤት ወንድም ዬቭጌኒ ስፒሪን ከ6,900 የአሜሪካ ዶላር በላይ እንዲቀጣ ወሰነ

ሐምሌ 28, 2020 በኢቫኖቮ ክልል የሚገኘው የፉርማኖቭስኪ ከተማ ፍርድ ቤት ወንድም ዬቭጌኒ ስፒሪን ጥፋተኛ ነው ብሎ ፈረደ። አቃቤ ሕጉ በወንድም ላይ የሰባት ዓመት እስር እንዲፈረድበት ጠይቆ ነበር። ፍርድ ቤቱ ግን ወንድም ዬቭጌኒ ስፒሪን 500,000 ሩብል (6,920 የአሜሪካ ዶላር) መቀጫ እንዲከፍል ወስኗል። ወንድም ዬቭጌኒ ስፒሪን ይግባኝ እንደሚጠይቅ ታውቋል።