ሰኔ 23, 2020
ሩሲያ
የሩሲያ ፍርድ ቤት ወንድም ዴኒስ ክሪስተንሰን የእስር ጊዜውን ሳይጨርስ እንዲለቀቅ ወሰነ
በኩርስክ ክልል የሚገኘው የለጎቭስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ሰኔ 23, 2020 ወንድም ዴኒስ ክሪስተንሰን የእስር ጊዜውን ሳይጨርስ እንዲለቀቅ ወሰነ። ዳኛው በአቃቤ ሕጉ ጥያቄ መሠረት ወንድም ዴኒስ በቀረው የእስር ጊዜ ፋንታ 400,000 ሩብል (5,759 የአሜሪካ ዶላር) ቅጣት ከፍሎ ነፃ እንዲሆን ወስነዋል። ውሳኔው በአሥር ቀናት ውስጥ ተፈጻሚነት ያገኛል፤ ከዚያ በኋላ ወንድም ዴኒስ ወደ ቤቱ ሄዶ ከሚስቱና ከእምነት ባልንጀሮቹ ጋር መገናኘት ይችላል። ለዚህ ድል ውዳሴ የሚገባው ይሖዋ ነው!