በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ዴኒስ ክሪስተንሰን መስከረም 2020 እስር ቤት ውስጥ ከጠበቃው ጋር ሲነጋገር

ጥቅምት 26, 2020
ሩሲያ

የሩሲያ ፍርድ ቤት ወንድም ዴኒስ ክሪስተንሰን የእስር ጊዜውን ሳይጨርስ እንዲፈታ የቀረበውን ጥያቄ በድጋሚ ውድቅ አደረገ

የሩሲያ ፍርድ ቤት ወንድም ዴኒስ ክሪስተንሰን የእስር ጊዜውን ሳይጨርስ እንዲፈታ የቀረበውን ጥያቄ በድጋሚ ውድቅ አደረገ

ጥቅምት 26, 2020 የልጎፍ አውራጃ ፍርድ ቤት ወንድም ዴኒስ ክሪስተንሰን የእስር ጊዜውን ሳይጨርስ እንዲፈታ የተላለፈውን ውሳኔ በድጋሚ ውድቅ አደረገ፤ ወንድም ዴኒስ ክሪስተንሰን ከታሰረ ሦስት ዓመት አልፎታል። ወንድም ዴኒስ ክሪስተንሰን በአሥር ቀን ውስጥ ይግባኝ መጠየቅ ይችላል። የተፈረደበት የእስር ጊዜ የሚያበቃው ግንቦት 2022 ነው። የእስር ጊዜው፣ ጉዳዩ በፍርድ ቤት ከመታየቱ በፊት የታሰረበትን ጊዜም ግምት ውስጥ ያስገባ ነው። ሆኖም ባለፈው ወር የእስር ቤቱ አስተዳደር የእስር ቤቱን ሕግ “ሆን ብሎ የሚጥስ ዓመፀኛ” በማለት ወንጅሎታል። ስለዚህ ለፍርድ ሳይቀርብ የታሰረበት ጊዜ ላይታሰብለት ይችላል፤ እንደዚያ ከሆነ ደግሞ ግንቦት 2022ም ከእስር ላይፈታ ይችላል።

ወንድም ዴኒስ ክሪስተንሰን ግንቦት 25, 2017 ከታሰረበት ጊዜ አንስቶ እሱም ሆነ ባለቤቱ አይሪና ይህ ነው የማይባል አካላዊ፣ አእምሯዊና ስሜታዊ ጫና ደርሶባቸዋል። ሆኖም ሁለቱም ደስታቸውን አላጡም፤ ይህን የእምነት ፈተና ለመቋቋም ያላቸውን ቁርጥ አቋምም ቢሆን አላላሉም። እንዲጸኑ የረዳቸው አንዱ ነገር በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ወንድሞችና እህቶች ስለ እነሱ የሚያቀርቡት ጸሎት ነው።