በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የካቲት 25, 2021
ሩሲያ

የሩሲያ ፍርድ ቤት የወንድም ሮማን ግሪዳሶቭን የአመክሮ ጥያቄ ውድቅ አደረገ

የሩሲያ ፍርድ ቤት የወንድም ሮማን ግሪዳሶቭን የአመክሮ ጥያቄ ውድቅ አደረገ

የካቲት 25, 2021 የኦረንበርግ ክልላዊ ፍርድ ቤት፣ ወንድም ሮማን ግሪዳሶቭ በአመክሮ እንዲፈታ የቀረበውን ጥያቄ ውድቅ አደረገ። በመሆኑም ወንድም ሮማን የፍርድ ጊዜው እስከሚያበቃበት እስከ ነሐሴ 2021 ድረስ እስር ቤት መቆየት ይኖርበታል። ወንድም ሮማን የታሰረው ከመስከረም 2019 አንስቶ ነው። ወንድም ሮማን የካቲት 2020 በእስር ቤት ጠባቂዎች ከተደበደቡት አምስት ወንድሞች አንዱ ነው።